Thursday, March 26, 2015

ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣኖች። ወደ አገራችን ክልሎች በሚንቀሳቀሱበት ግዜ ኔት-ዎርክ እንዲቋረጥ ስለሚደረግ። ህዝቡ እለታዊ ስራዎችን እንዳያሳልጥ እየተቸገረ መሆኑን ተገለፀ፣



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። የኢህአዴግ ቡድን ከፍተኛ አመራሮች። ከኢትዮጵያ ህዝብ እየተነጠሉ መሆናቸውን ስላወቁ። ወደ ክልሎች ሲሄዱ ለደህንነታቸው በመስጋት። የቴለፎንና የኢንተርኔት ግንኝነት እንዲቋረጥ ማድረግ የተለመደ የአሰራር ዘዴአቸው አድርገው እየተጠቀሙበት እንደሆኑና። በዚህም ምክንያት ህብረተሰቡ እለታዊ ስራዎችን እናዳያሳልጥ ተቸግሮ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፣
    በዚህም መሰረት። ህዝቡ እየተፈጠረ ያለውን ችግር አስመልክቶ  ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጥያቄውን ባቀረበበት ሰዓት። ግዚያዊ የቴክኒክ ችግር ስላጋጠመን ነው ቶሎ ብለን እንፈታዋለን እያሉ  ህዝቡን ሊያታልሉት ቢሞኩሩም። ህብረተሰቡ ግን ስርዓቱ ሆን ብሎ የኔት ወርክ መቆራረጥ እንዲፈጠር ማድረጉን ነቅተንበታል።    “ እስከመቼ ነው እንደዚህ ሁነን መኖር የምንችለው” በማለት። ብሶቱን በመግለፅ ላይ እንደሚገኝ የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል፣