Sunday, March 1, 2015

በአማራ ክልል የሚገኙ የክልልና የዞን አመራሮች በተለያዩ ወረዳዎች በመግባት እያደረጉት ያለ ቅስቀሳ ተቀባይነት እንዳላገኘ የደረሰን መረጃ አመለከተ።



    በአማራ ክልል በሁሉም ወረዳዎች የተፈጥሮ ሃብት ልማት በሚል አጀንዳ የምረጡን ቅስቀሳ ማድረጋቸውና በርካታው ህዝብ ግን ተወዳዳሪ በሌለበት ማንን ለንመርጥ ነው የምንመዘገበው ይልቁንስ ይህንን ምርጫ ተከትሎ ያንጃበበውን የመልካም አስተዳደር ችግር መቅረፍ ብትችሉ ይሻላል ብለው መቃወማቸውና በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች በአስመራጭነት የተቀመጡ ዜጎችም የቀበሌና የወረዳ አስተዳዳሪዎች ጣልቃ እየገቡ ሊያሰሩን አልቻሉም ሲሉ የባንጃ ወረዳ የወትለሃ ቀበሌ ምርጫ ጣቢያ አስመራጮች ራሳቸውን ማግለላቸውን የደረሰን መረጃ አስረድቷል።
     በክልሉ ባህርዳር ከተማ ጥር 21 እና ጥር 22 ቀን  2007 ዓ/ም በሙሉዓለም አዳራሽ በ አነስተኛና ጥቃቅን ስራዎች የተደራጁ የባህርዳር ዙሪያና የከተማው ወጣቶች በዞኑ የድርጂት ጉዳይ ሃላፊ በጅብሪል አህመድ የተመራውን የምረጡን ስብሰባ ወጣቶቹ ረግጠው መውጣታቸውን ጨምሮ ገልጿል።
    በተጨማሪም ጥር 24/ 2007 ዓ/ም ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር ከተማ ለመንፈሳዊ ስብከት የመጡት እነ መምህር ዘመነን በርካታ ፖሊሶች በጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከመእመናኑ ጋር ቁጭ ብለው እየጠበቋቸው እንደነበሩ መረጃው አክሎ አስረድቷል።