Sunday, March 29, 2015

በሰሜን ጎንደር ዞን የትክል ድንጋይ ከተማ ነዋሪዎች በወያኔ ኢህአዴግ ስርአት ላይ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳካሄዱ ምንጮቻችን ከአካባቢው ገለፁ፣



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የትክል ድንጋይ ነዋሪዎች የሆኑት ዜጎቻችን። እያጋጠማቸው የቆየው የማህበራዊ አገልግሎት ችግር መፍትሄ እንዲደረግላቸው በተደጋጋሚ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀረቡትን አቤቱታ። ዛሬ ነገ በማለት ሰሚ ጆሮ ስላጡ የካቲት 14 2007 ዓ/ም በገዢው ስርአት ላይ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እዳካሄዱ ታወቀ፣
  መረጃው በማከል። ነዋሪዎቹ ባካሄዱት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ካሰሟቸው  መፎክሮች ገሚሶቹን ለመጥቀስ ያህል። ህዝብ በውሃ ወለድ በሽታ ለሞትና ለስቃይ እየተዳረገ ነው፤ በመሰረት ልማት ዝርጋታ ላይም። በደርግ ዘመነ መንግስት የተሰራ ካልሆነ በስተቀር። የተደረገ ለውጥና ብቃቱን የጠበቀ ስራ የተሰራ አዲስ ነገር የለም የሚሉና ሌሎችም መፎክሮች እያሰሙ ወደ ከተማው ከንቲባ ፅህፈት ቤት ቻላቸው አማሃ በመሄድ ጥያቄያቸውን ባቀረቡበት ጊዜ በህዝቡ ተቃውሞ የተደናገጠው የከተማዋን ከንቲባ በበኩሉ። መሰረተ ልማት አለ የቀረ ካለ ግን ቀስ በቀስ እናሟላለን በማለት የህዝቡን ተቃውሞ ለማረጋጋት ሲል የማይተገበር መልስ እንደመለሰላቸው ለማወቅ ተችሏል፣