Friday, April 17, 2015

በመረብ ለኸ ወረዳ፤ ምኹዓት ሳዳ በተባለው አካባቢ የሚኖሩ ዜጎቻችን። በፖሊሶችና በወታደራዊ አዛዦች ግፍ እየደረሰባቸው መሆኑን ምንጮች ከቦታው ገለፁ፣



በትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ መረብ ለኸ ወረዳ፤ ምኹዓት ሳዳ በተባለው አካባቢ የሚኖረው ህዝብ። በተለይ ወጣቶች የፈፀሙት ወንጀል ሳይኖራቸው። በአካባቢው በሰፈሩት የኢህአዴግ ቡድን የመከላከያና የፖሊስ አዛዦች። ለምን በቡድን ሁናችሁ ትንቀሳቀሳላችሁ በሚል ሰንካላ ምክንያት። በላያቸው ላይ ድብደባ እየፈፀሙባቸው እንደሆኑ። ምንጮቻችን ከአካባቢው አስረድተዋል፣
    በምኹዓት ሳዳ ነዋሪዎችና በአካባቢው ህዝብ ላይ ኢ-ሰብአዊ ግፎችን እየፈፀሙ ከሚገኙት ቅጥረኞች ውስጥ።- በጠራውር ቀበሌ ውስጥ ተመድበው እየሰሩ ከሚገኙት። ተስፋይ ወይም ዓዲ ኣርባዕተ በሚል ቅጥያ ስም የሚጠራና ምሩፅ የዕብዮ በተባሉ ፖሊሶች እንዲሁም የ31 ክፍለጦር አባላት የሆኑት ሻንበል ጓሳይ፤ ሻምበል ፅጋቡ ወዲራያና ሌሎችም ታጣቂዎች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፣