በምንጮቻችን መረጃ መሰረት።-በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ላዕላይ አድያቦ
ወረዳ፤ ጤርር በተባለ ቦታ የሚገኙ የወታደር አመራሮች። የአካባቢው ነዋሪ ህዝብ ከመጋቢት ወር አጋማሽ 2007 ዓ.ም ጀምሮ ከ11 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ እንዳልቻለና ጥዋትም ሁለት ሰዓት ሳይሞላ
ከቤታቸው እንዳይንቀሳቀሱ የሚከለክል አዲስ መምሪያ በማፅደቅ የአካባቢው ህብረተሰብ ዕለታዊ ስራውን እንዳያሳልጥ እንቅፋት ፈጥረውበት
እንደሚገኙ ታወቀ፣
በዚህም ምክንያት የአካባቢው ነዋሪ ህብረተሰብ ከቤቱ ሲወጣ ጀምሮ በወታደሮቹ
ፍተሻ እንደሚደረግበትና በስጋት አይን ስለሚመለከቱት እጅግ በአስከፊ የኑሮ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ምንጮቻችን አክለው ገልፀዋል፣