የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው። አቶ ሙላቱ
የተባለ ነዋሪነቱ አዲስ አበባ ትውልዱ ደግሞ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የሆነ ዜጋ። መጋቢት 26/2007 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ሳታላይት
ቴሌቭዥን /ኢሳት/በሞባይል ደውለህ መረጃ ሰጥተኃል በማለት በኢህአዴግ
ካድሬዎች ከመኖርያ ቤቱ በሌሊት ተጠልፎ በሰንሰለት ታስሮ እንደተወሰደ ሊታወቅ ተችሏል፣
አቶ ሙላቱ በሞባይል ደውሎ ለኢሳት ቴሌቭዥን መረጃ ሲሰጥ በቴሌኮሚንኬሽን ተቆጣጠርነው በሚል የሃሰት ክስ። በስርዓቱ ካድሬዎች ከሚኖርበት
ቄራ ከተባለው ሰፈር ከወሰዱት ቀን ጀምሮ እስካሁን ያለበት ቦታ በወል እንደማይታወቅ የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል፣