ያገነኘው መረጃ እንዳመለከተው። በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኝ ህዝባችን በመኖሪያ ቤቶች እጥረት ተቸግሮ እንደሚገኝ የገለፀው መረጃው።
የወያኔ/ኢህአዴግ ብዱን የቤቶችን እጥረት ለመፍታት የኮንዶሚኒየም ቤቶች እየሰራሁ ነኝ በማለት የሚያቀርበውን የመደናገሪያ ቅስቀሳ
በተግባር የሚገለፅ ባለመሆኑ። በርካታ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤት አጥተው በከባድ ችግር ላይ ወድቀው እንደሚገኙ
ለማወቅ ተችሏል፣
እየተሰሩ ያሉት የኮንዶሚንየም ቤቶች። ከነዋሪው ህዝብ ጋር ሲነፃፀር በጣም
አነስተኛ መሆኑና። አንድ መኝታ ክፍል ያለው ቤት የሚፈልግ ሰው መጀመሪያ 35ሺ ብር እንዲከፍል ሲገደድ በየወሩ ደግሞ 1.800ብር
እንዲከፍል፤ ለባለ ሁለት መኝታ ክፍል ቤት ደግሞ መጀመሪያ 65ሺ ብር እንዲከፈልና በየወሩም 2.800 ብር እንዲከፍል፤ ባለ 3ት
መኝታ ክፍል ቤት የሚፈልግ ደግሞ መጀመሪያ 91ሺ ብር በየወሩ ደግሞ 5ሺ ብር እንዲከፍል እንደሚገደድ መረጃው አስረድቷል፣
ይህ አሰራር ለድሃው ህብረተሰብ ግምት ውስጥ ያላስገባ በመሆኑ። መኖሪያ
ቤት የሚፈልግ ሰው የሚከፍለው ገንዘብ ስለሚያጣ ቤት የማግኘት እድሉ
የተዘጋበት እንደሆነና። በተሰራው የኮንዶሚንየም ቤትም መጀመሪያ እድሉ የሚሰጠው የኢህአዴግ አባል መሆን እንደሚጠበቅበትና ለኢህአዴግ
የማይደግፍ ከሆነ ግን በጉቦና በቤተሰብ አሰራር ስለሚፈጸም። በዚህም ጉልህ የሆነ የወገንተኝነት ተግባር እንደምታይበት መረጃው ጨምሮ
አስረድቷል፣