በመረጃው መሰረት በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የአዲግራት
ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመጪው ግንቦት ወር 2007 ዓ/ም በሚከሄደው የይስሙላ ምርጫ ላይ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን እንዲመርጡ በዩኒቨርሲቲው
ፕረዝዳንት ዶክተር ዛይድ ነጋሽና በምክትሉ ዶክተር ዘላለም ቅስቀሳ እየተደረገላቸው ሲሆን። ተማሪዎች የሰጡት መልስ ግን እናንተ
አስተማሪዎች ናችሁ ወይስ የስርዓቱ ካድሬ በማለት እንደተቃወሟቸው ታውቋል፣
የዩኒቨርሲቲው መምህራን በብኩላቸው የሆነ አቅመ-አዳም የደረሰ ሰው የራሱ
የፖለቲካ አላማ አለው እኛም ብንሆን የራሳችን የሆነ የፖለቲካ አመለካከት አለን ብለው መልስ ከሰጡ በኋላ የዩኒቨርሲቲው ባለስልጣናት
በበኩላቸው ካሁን በኋላ የተቃወመ ተማሪ እስከ መባረር የሚደርስ እርምጃ እንወስድበታለን በሚል እያስፈራሯቸው መሆናቸውን ለማወቅ
ተችሏል፣
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በሚጠጣ ውሃ እጥረት ሲሰቃዩ
መቆየታቸውንና መፍትሔ እንዲደረግላቸው በተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያቀርቡም ምንም አይነት ለውጥ ሊመጣ ባለመቻሉ ምክንያት። በስርዓቱ ላይ
ያላቸውን ጥላቻ በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣