በበራህሌ ወረዳ ውስጥ የንግድ ድርጅቶች ከፍተው እየሰሩ ያሉትን የትግራይ
ተወላጅ የሆኑ ዜጎቻችን በወረዳው አስተዳዳሪዎች በተተመነው ዋጋ መሸጥ ካልቻላችሁ እርምጃ ይወሰድባችኃል የሚል ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው
መሆኑን የገለጸው መረጃው ነጋዴዎቹ በበኩላቸው ለአንድ ኪሎ ስኳር በ40 ብር፤ ለአንድ ኪሎ ቡና በ120 ብር ገዝተን ምን ልናገኝበት
ነው እናንተ በምትሉት ዋና የምንሸጠው በማለት መቃወማቸውን የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
በተመኑ መሰረት እንዲሸጡ መመሪያ የተሰጣቸው ሰዎች ወደ ወረዳው አስተዳደር
ቀርበው ምን ሰርተን ለመኖር ትፈልጉናላችሁ ብለው ብሶታቸውን ቢያቀርቡም ከዚህ በላይ መሸጥ ከፈለጋችሁ ወደ ክልላችሁ ሂዱ የሚል
መልስ መሰጠታቸውና መጨረሻም ወደ ትግራይ ክልል ባለስልጣኖች አቤቱታቸውን አቅርበው ሰሚ አካል ባለማግኘታቸው ምክንያት ስራቸውን
ለማቆም እንደተገደዱ መረጃው አክሎ አስረድቷል።