Sunday, April 26, 2015

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች ጥራቱን ያልጠበቀ ምግብ አንመገብም በማለት ተቃውሞ ሊያደርጉ ሞክረው እንደተከለከሉ ተገለፀ።




      መቐለ ዩኒቨርሲቲ እየተማሩ ያሉት ተማሪዎች ጥራቱን ያልጠበቀ ምግብ እየቀረበልን ነው በማለት እያማረሩ እንደቆዩ የገለጸው መረጃው ባለፉት ቅርብ ቀናትም ለምንድነው ጥራቱን ያልጠበቀ ምግብ እያቀረባችሁ ለበሽታ የምታጋልጡን በማለት ተቃውሞ ለማካሄድ በሞከሩበት ጊዜ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚገኙ ካድሬዎች ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን እንደከለከሏቸው ለማወቅ ተችሏል።
      መረጃው በማከል በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች የአስተዳደርና የምግብ ጥራት ጉድለት እንዲስተካከል የሚጠራ የተቃውሞ ሰልፍ ያካሄዱ ቢሆኑም እስከ አሁን ደረስ ግን ችግራቸውን ሰምቶ መልስ የሚሰጥ የመንግስት አካል እንዳላገኙ ታወቀ።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ ማንኛውም የአዲግራት ነዋሪ ህዝብ ወይን ጋዜጣ ገዝቶ መያዝ እንዳለበትና ይህን ማድረግ ያልቻለ ግለ ሰብ ደግሞ በገዢው ስርአት የሚሰጥ የእለታዊ ሸቀጣሸቀጦችን እንደ ዘይት፤ ስዃርና የፊኖ ዱቄት የመሳሰሉትን እንዳያገኝ መከልከሉን የተገኘው መረጃ አስታውቋል።