Saturday, April 25, 2015

ገዥው አምባገነኑ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት በባህር ዳር ከተማ የጣና ፎረም ስብብሰባ እያካሄደ መሆኑን ተከትሎ ተላላኪ የፌድራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በህዝቡ ላይ ከባድ ቁጥጥር እያደረጉ መሆናቸው ተገለፀ፣



የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው አምባገነኑ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት በባህር ዳር ከተማ ጣና መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ሚያዝያ 10 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ  የጣና ፎረም ስብሰባ  በባህር ዳር ከተማ ጣና መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ሲሆን ይህንን ተከትሎም በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የስርዓቱ ተላላኪ  የፌድራል ፖሊስ አባላትና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተሰማርተው በነዋሪው ህዝብ ላይ ከባድ ቁጥጥር እያደረጉ መሆናቸውንና ከባህርዳር ጎንደር ከባህር ዳር አዴት ከባህር ዳር ፍኖተሰላምና ከባህርዳር ወደ ጣና ሃይቅ ገዳማትና ሌሎች አካባቢዎች በሚወስዱ መንገዶች ላይ የፍተሻ ኬላዎች መቋቋማቸውን ለማወቅ ተችሏል፣    
    በእነዚህ  በከተማዋ መግቢያና መውጫ መስመሮች በተቋቋሙ  አዳዲስ የፍተሻ ኬላዎች እየተደረጉ ባሉ ፍተሻዎች መታወቂያ ያልያዙ ወጣቶች እየታሰሩ መሆናቸው መረጃው አክሎ አስረድቷል፣