እንደመረጃው ገለፃ በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ አጠቃላይ የመስሪያ ቤት ሰራተኞች ሚያዝያ 7 ቀን 2007 ዓ/ም በአቅም ግንባታ ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊዎች መድረክ መሪነት የመልካም አስተዳድር
ስልጠናዎች የተካሄዱ ሲሆን ከተሰብሳቢዎች በርካታ ጥያቄዎች በተቃውሞነት
መነሳታቸውን ታውቀዋል፣
እንደ አብነት በአዲስ ከተማ፤ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል።- ሲቪል ሰርቫንቱ
ባልተዘጋጀበት ሁኔታ የመልካም አስተዳደር ስልጠና መሰጠቱ ለመጪው ምርጫ ታስቦ እንጂ ለእድገት አይደለም?፥ የመንግስት ሰራተኛው
የኑሮ ሁኔታ አሰቃቂ ደረጃ ላይ ነው ያለው፥ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላን በተመለከተ መንግስት በከተማችን ከ18 ሺህ በላይ ካሉት
የመንግስት ሰራተኞች መካከል ለ10 ሺ ሰራተኛ ቤት አድያለሁ ማለቱ ፍፁም ውሸት ነው፥ ቢ.ኤስ.ሲ’ና ቢ.ፒ.አር በቀጥታ ከአደጉ ሃገሮች ኮፒ መደረጋቸው ስህተት ነው ስለሆነም ሰራተኛውን
በትክክል መገምገም አይችልምና የሙስና መስፋፊያነት መንገዶችን መንግስት እየደገፈ ነው የሚሉት ተነስተው። መድረኩን ይመራ የነበረው የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ ተዘራ የተባለ የስርአቱ
ተላላኪ የቀረቡትን ጥያቄዎች ለመመለስ ተቸግሮ ለክፍለ ከተማው የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ማስተላለፉ ታውቋል፣