Wednesday, April 1, 2015

በፀገዴ ወረዳ የሚገኙ ካድሬዎች የዳንሻ ነዋሪዎችን ሰብስበው ለህወሃት አባልነት የገንዘብ መዋጮ እንዲያዋጡ በጠየቁበት ግዜ ተቃውሞ እንዳጋጠማቸው ታወቀ፣



በትግራይ ምእራባዊ ዞን። ፀገዴ ወረዳ የሚገኙ የስርዓቱ ካድሬዎች። የዳንሻና አካባቢው ነዋሪዎችን። መጋቢት 7/ 2007 ዓ/ም ሰብስበው። የአባልነት ገንዘብ እንዲከፍል በጠየቁበት ሰዓት። ተሰብሳቢዎቹ በበኩላቸው። ከዚህ በፊት ለየካቲት 11 ያዋጣነውን ገንዘብ ለግል  ጥቅማችሁ በማድረጋችሁ  ልታፍሩ ይገባል። ካሁን በኋላ ገንዘብ ብላችሁ እንዳትጠይቁን። የሚል መልስ እንደሰጧቸው ለማወቅ ተችሏል፣
    የዳንሻ ከተማ ነዋሪ ህዝብ። ለየካቲት 11 ተብሎ የተዋጣው ገንዘብ በምን ስራ ላይ እንደዋለ። ያለምንም ደረሰኝ ተቀብላችሁ ገቢውንና ወጪውን ሳታሳውቁ ገንዘቡን አጠፋፍታችሁታል በማለት። በካድሬዎቹ ላይ እምነት እንደሌለው በምሬት መናገሩን መረጃው አክሎ አስረድቷል፣