ምንጮቻችን ከአካባቢው የላኩት መረጃ እንደሚያመለክተው በከፋና አካባቢው
የሚኖሩ የህዝብረተሰብ ክፍሎች በዚህ ሳምንት በደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳደር የተመራ ስብሰባ እንደተካሄደላቸውና የስብሰባው አጀንዳም
በመጪው ምርጫ ደህዴን/ኢህአዴግን ምረጡ የሚል ቅስቀሳ መሆኑንና ተሰብሳቢው ህዝብም በስልጣን ላይ ያለው ስርአት ለህዝብ የሚረባ
መሰረተ ልማት ሊሰራ ባለመቻሉ ምክንያት በአካባቢው የሚመረቱት እንደ ቡና እና ሌሎች ምርቶችን ወደ ገበያ ለማቅረብ እጅግ ተቸግሮ
እንደሚገኝና ላልተፈለገ ኪሳራና እንግልት መጋለጡን አብራርተዋል።
በተጨማሪም በደቡብ ክልል ሩቅ አካባቢ የሚኖር ህዝብ ከማንኛው የማህበራዊ
አገልግሎት ርቆ የሚኖር ሲሆን የከፋ ህዝብም የሃብታም መሬት ባለቤት ሁኖ እያለ የመሰረተ ልማት ተጠቃሚ አለመሆኑ እንደ ቡና እና
ሌሎች ምርቶችን አምርቶ ለገበያ የሚያቀርብበትን የመኪና መንገድ መንግስት ባለመዘርጋቱ የአካባቢው ህዝብ በድህነት አረንቛ ውስጥ
እየኖርን ነው በማለት በስርአቱ ላይ ያለውን ብሶት እየገለፀ እንደሚገኝ
መረጃው አክሎ አስረድቷል።