በአማራ ክልል የሚገኙ ባልስልጣኖች በመጪው
ግንቦት ወር በሚካሄደው የይስሙላ ምርጫ ህዝቡ እንዲመርጣቸው ያካሄዱት ቅስቀሳ በህዝብ ተቀባይነት በማጣቱና በስርዓቱ ላይ እየተካሄደ
ያለው ተቃውሞ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ሊመርጡ ይችላሉ በሚል የጠረጠሯቸውን ንፁሃን ዜጎች ንብን የያዘ ፖስተር
ቀድዳችኋል በማለት እያሰሯቸው መሆናቸው ሊታወቅ ተችሏል።
ንብ ያለበትን በራሪ ወረቀት ቀደዳችሁ በሚል ከታሰሩት ወገኖች መካከል የተወሰኑትን
ለመግለፅ ያህል ሙስጠፋ አሊ ነዋሪነቱ ደቡብ ወሎ ዞን ቦረና፥ መኩየ ሃይሉ ከባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 03፥ ታደሰ ጌቱ ከላሊበላና
ሌሎችም መሆናቸውና ህዝቡ በላዩ ላይ እየወረደ ያለውን ግፍ ተቋቁሞ በኢ.ህ.አ.ዲ.ግ አንገዛም በማለት ተቃውሞው እየቀጠለ መሆኑን
ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሰን መረጃ አስረድቷል።