Saturday, April 18, 2015

በአማራ ክልል የሚገኙ የብአዴን/ኢህአዴግ ካድሬዎች በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ መምህራንን በመሰብሰብ የምረጡን ቅስቀሳ እያደረጉላቸው እንደሚገኙ ታወቀ፣



   ከመጋቢት 28/2007ዓ/ም ጀምሮ በሁሉም የአማራ ክልል የሚገኙ መምህራን ከስራዎቻቸው በማደናቀፍ በብአዴን/ኢህአዴግ መሪዎች ቅስቀሳ እያካሄዱባቸው እንደሚገኙ የገለፀው መረጃው። መምህራኖቹ የስርአቱ የአስተዳደር ችግር በርካታ ሃሳቦች ባነሱበት ጊዜ። ሁሉም የተነሱ ጉድለቶች የኛ ችግሮች ናቸው። ይሁን እንጂ በሚቀጥለው ምርጫ ላይ ከመረጣችሁን እናስተካክለዋለን የሚል መልስ እንደስጧቸው  ለማወቅ ተችሏል፣
    መምህራኑም በበኩላቸው እናንተን ታስተካክላላችሁ ብለን ተስፋ ማድረግ ”ከዝንብ ማር መጠበቅ“ እንደማለት ነው፣ በናንተ አስራር ተስፋ የቆረጡ መምህራን ሰራዎቻቸውና ሃገራቸውን ትተው  ወደ ስደት የሚሄዱ ያሉት ሲሉ እንደገለፁላቸውና የተካሄደው ስብሰባም ያለምንም ፍሬ እንደተበተነ ለማወቅ ተችሏል፣