Saturday, May 9, 2015

በትግራይ ክልል የሚገኙ የፖሊስ መኮንኖች በመርጫ ወቅት ህዝቡን አፍነው ለመያዝ ዒላማ ያደረገ በአዲግራት ከተማ ውስጥ ተከታታይ ስብሰባ እንዳደረጉ ተገለፀ።




በትግራይ ክልል የሚገኙ ከረዳት ኢንስፔክተር በላይ የሆኑት የፖሊስ መኮንኖች ለስድስት ቀናት ያህል በአዲ ግራት ከተማ ውስጥ ዘአማንኤል ለገሰ (ወዲ ሻንበል)ና ሓዱሽ ዘነበ በተባሉ የትግራይ ክልል የፀጥታ ሃላፊውች  በተመራው ስብሰባ ላይ ህዝቡ ስለ ጠላን በምርጫው ጊዜ ዓመፅ እንዳያነሳ ጥብቅ ክትትል ማድረግ አለብን፤ ለሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶችም እንዳይመርጥ በማስፈራራት ኢህአዴግን እንዲመርጥ ማድረግ ይገባናል፤ ዛሬ ህወሃት ኢህአዴግን እንዣብቦት ካለው የመውደቅ አደጋ ማዳን ይጠበቅብናል የሚሉና ሌሎች መመሪያዎች መወረዳቸውን የተገኘው መረጃ አስረድቷል።
    መረጃው ጨምሮ ህዝቡ እያማረረባቸው ያሉትን ነጥቦች ለጊዜው ተስፋ  በመስጠት እናረጋጋው በሚል መወያየታቸውና ህዝቡ እያማረረባቸው ካሉት ነጥቦችም በፍትህ፤ መልካም አስተዳደር፤ ግብር አከፋፈል፤ በመኖርያ ቤቶች አሰጣጥና የመሳሰሉት እንደሁኑ የገለፀው መረጃው ህዝቡ እያነሳቸው ባለው ቅሬታዎች ላይ በምን አይነት መልኩ ብንሄድበት ይሻላል፤ ምንስ ማድረግ መቻል አለብን በሚሉ ላይም መወያየታቸውና መርጫው እስከሚያልፍ ድረስም ህዝቡን ሊያረጋጉ የሚችሉ የተስፋ ቃላቶች ማቅረብ ይገባናል በማለት ስብሰባቸውን እንደጨረሱ መረጃው አክሎ አስረድቷል።