Thursday, June 18, 2015

በወረኢሉ ወረዳ ሰሞኑን በተሰጠው የ10ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና ላይ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ተማሪ ብርሃኑ ቦጋለ ከፈተናው እንደተባረረ ምንጮቻችን ገለፁ።



   በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ ሰሞኑን በተሰጠ የ10ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና ላይ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ተማሪ ብርሃኑ ቦጋለ ምንም አይነት ጥፋት ሳይኖረው ከሌሎች ተማሪዎች ኮርጀሃል በሚል ስምን የማጥፋት ውንጀላ በስርዓቱ ካድሬዎች ወደ ወረኢሉ እስር ቤት ተወስዶ እንደታሰረ ሊታወቅ ተችሏል።
   ምንጮቻችን አክለው እንደገለፁት- የኢህአዴግ ባለስልጣኖች ከምርጫ ማግስት ጀምረው በሌሎች ፓርቲዎች ለተሳተፉና አባል በሆኑ ዜጎቻችን ላይ የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠሩ በማሰር እኩይ ተግባር ላይ የተሰማሩ ሲሆን በተለይ ደግሞ በተማረው የሰው ሃይል ላይና ትምህርቱን በመከታተል ላይ ባለው የህብረተሰብ ክፍል ላይ ትኩረታቸውን በማድረግ በገዛ ሃገሩ ትምህርቱን በነፃነት እንዳይከታተል እያሸማቀቁት እንደሚገኙ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ አስረድቷል።