Thursday, June 18, 2015

በአዲስ አበባ ከተማ የ4 ኪሎ ትምህርት ቤት መምህር የሆነው ስዩም ዘሩ የተባለ ወገን በሃገራችን የሚካሄደው ምርጫ ለኢህአዴግ ፓርቲ የስልጣን ሽግግር ተብሎ የሚካሄድ እንጂ ሌላ ለውጥ አያመጣም ብለህ ተማሪዎችን ሰብስበህ ተናግረሃል ተብሎ እንደታሰረ ተገለፀ።



        ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ እንደሚያመለክተው የሃገራችን ዋና ከተማ በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ 4 ኪሎ ት/ቤት ያስተምር ለነበረው የሰሜን ወሎ ዞን የላሊበላ ከተማ ተወላጅ የሆነውን ስዩም ዘሩ ግንቦት 23/2007 ዓ.ም በሃገራችን እየታየ ያለው ምርጫ ምንም አይነት ለውጥ አያመጣም።
 አሁን ሃገራችንን እየመራ ያለውን ፓርቲ ለማጀብ ካልሆነ በስተቀር ብለህ በክፍል ውስጥ ለሚማሩ ተማሪዎች ቀስቅሰሃል ተብሎ ከተወነጀለ በኋላ የኢህአዴግ አባል እንዲሆን ተጠይቆ አልፈልግም በማለቱ ብቻ ከሚያስተምርበት ክፍል ተወስዶ እንደታሰረ ሊታወቅ ተችሏል።
     የደረሰን መረጃ እንደገለፀው የኢህአዴግ ባለስልጣናት በነሱ መስመር ላልተጓዘና የፓርቲያቸው አባል አልሆንም ላለ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የተለያዩ የተንኮል ሴራዎችን እየጎነጎኑ ስሙን በማጥፋት በህብረተሰቡ ዘንድ እንዲጠላና በስነ ልቦናው ላይም ሆነ በማህበራዊ ህይወቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱበት እንደመጡና አሁንም እየቀጠሉበት እንደሚገኙ ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።