በደረሰን መረጃ መሰረት በአማራ ክልል የሚገኙት የህክምና ሙያተኞችና መምህራኖች
ስብሰባው ኢዴሞክራሲያዊ አሰራር የተከተለ እንደሆነና በተለይም ከምርጫ ጋር አያይዘው በሃገሪቱ ሰላም፤ ልማትና መልካም አስተዳደር
እንዳይመጣ ምክንያት የሆነው የእናንተ ፀረ ዴሞክራሲያዊ ተግባር ነው፤ በህክምናም ሆነ በትምህርት ቤት ውስጥ ይህን አሰራር ተቀብለን
ተግባራዊ አናደርግም ከፈለጋችሁ ዛሬውኑ አባሩን በማለት የተናገሩ ሲሆን የክልሉና የስቪል ሰርቢስ ተወካዮች በየደረጃው በስብሰባው
ላይ ተገኝተው ሃሳብ ቢሰጡም የተቀበላቸው አካል እንደሌለ መረጃው
ጨምሮ አስረድቷል።
በአሁኑ ሰዓት ስርዓቱ ባስቀመጠው አፋኝ የአደረጃጀት መዋቅር ሁሉም የመንግስት
ሴክተሮች በነፃነት የመስራት መብታቸው የተነፈገ እንደሆነና መንግስት የራሱን እድሜ ለማራዘም ሲል በሚፈልገው መንገድ ብቻ እንዲሄዱ
የሚያስገድድ አሰራር በመከተሉ ምክንያት ሰራተኛውና ስርዓቱ ሆድና ጀርባ የሆኑበት ሁኔታ እንዳለ ባለፈው የዜና እወጃችን መግለፃችን
ይታወቃል።