Thursday, June 18, 2015

በታህታይ አዲያቦ ወረዳ ቢያራ በተባለ ቦታ ላይ ተክላይ ማዕሾ የተባለውን አርሶ አደር የትህዴን አባል ነህ በሚል ምክንያት በኢህአዴግ የፀጥታ አባላት እንደታሰረ ተገለፀ።



የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው- በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ታህታይ አድያቦ ወረዳ ልዩ ቦታ ቢያራ በተባለው አካባቢ በግብርና ስራ ይተዳደር ለነበረው ተክላይ ማዕሾ የተባለውን ግለሰብ ለ12 ቀናት በዚህ አካባቢ አልታየህም ትህዴን ወደ ተባለው ድርጅት ሂደህ ሰንብተህ ነው የመጣኸው በሚል የሃሰት ውንጀላ ግንቦት 22/2007 ዓ.ም ከምሽቱ 2፣00 ሰዓት ላይ ከመኖርያ ቤቱ ይዘው ወደ ባድመ እንደወሰዱት ምንጮቻችን አመለከቱ።
  ይህ በእንዲህ እያለ የህወሃት ኢህአዴግ ባለስልጣኖች በተለያዩ የሃገራችን የጠረፍ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ የዕለት እንጀራውን ለሚፈልግ ዜጋ ሰብአዊ መብቱን በተጋፋና በጣሰ  መልኩ እያሰሩ አሰቃቂ የግርፋትና የምርመራ ድርጊቶችን እየፈፀሙ እንደሚገኙ ምንጮቻችን አክለው  ገልፀዋል።