Monday, August 24, 2015

የትግራይ ህዝብ ከነሃሴ 1/2007 ዓ/ም ጀምሮ በህወሃት ካድሬዎች የተዘጋጀውን አጀንዳ ያለፍላገቱ እንዲወያይ በተደጋጋሚ ስብሰባ ላይ መጠመዱን ተገለፀ።



    የህወሃት ካድሬዎች ለመላው የትግራይ ህዝብ በተለያየ ቦታዎች በመሰብሰብ በመጪው 5 ዓመት በኢህአዴግ የተሰሩትን የልማት ስራዎች የሚሉ ፅሁፎች በማቅረብ ህዝቡ ስራውን ትቶ ስብሰባ ላይ እንዲውል እያስገደዱት ቢሆንም ህዝቡ ግን የተዘጋጀውን ፅሁፍ የናንተን በጎ አሰራር ብቻ የሚገልፅ እንጂ አብዛኛውን ደካማ ጎናችሁን ወደ ጎን ያስቀረ በመሆኑ ይህን አስመልክተን ግዜአችንን ማጥፋት አይገባንም በማለት እንዳልተቀበለውና ሙሉ በሙሉ እንደተቃወመው ለማወቅ ተችሏል።
    በተለይ የአክሱምና የዓድዋ ከተማ ነዋሪዎች ተዘጋጅቶ የቀረበውን ፅሁፍ “ጥቂት ስራወቻችሁን ሰማይ ላይ በማድረስ የሚገልፅ እንጂ በህዝቡ ላይ የተፈፀመው መሬትን የመንጠቅ እርምጃ፤ ብልሹ አሰራር፤ ፍትህ ያለመኖር፤ ከስርዓቱ እድሜ አንፃር የመሰረተ ልማት እድገቱ እንደማይመጣጠን፤ በህወሃት ኢህአዴግ የእድሜ ስልጣን ለራሳችሁና ለቤተሰቦቻችሁ ተጠቀማችሁ እንጂ ህዝቡን አልጠቀማችሁትም፤ በሚል በስብሰባው ላይ ከባድ ተቃውሞ ማጋጠሙና እስከ ስብሰባ መፍረስ ደረጃ መድረሱን ታውቋል።
    በተነሳው ተቃውሞና ግርግር ምክንያት ስብሰባው መቀጠል ስላልቻለ ይህን ለማረጋገት ሲባል የትግራይ ክልል የበላይ ባለስልጣኖች አቶ ኪሮስ ቢተውና አቶ ቴድሮስ ሃጎስ ነሃሴ 2/2007 ዓ/ም በሁለቱም ከተሞች እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸውና በ12ኛው የህወሃት ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ ሰዎች ከእያንዳንዱ ቀበሌዎች አንድ አንድ ሰው እንደመለመሉ  መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።