Sunday, August 2, 2015

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ መቱ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የቆዩ አንዳንድ ተማሪዎች በምርጫ ወቅት ተቃዋሚ ደግፋችኋል በሚል ሰንካላ ምክንያት ከምረቃ እንደታገዱ ሊታወቅ ተችሏል።



    በመቱ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ ቆይተው በዚህ ዓመት ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ ከ50 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች በፖለቲካ አመለካከታቸው እየታዩ በምርጫ ጊዜ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን መርጣችኋል በሚል ምክንያት እንዳይመረቁ የተከለከሉ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው ተማሪዎች በበኩላቸው እገዳው እንዲነሳላቸው ወደ ሚመለከታቸው አካላትና የትምህርት ክፍል ሃላፊዎች ቢያቀርቡም አቤቱታቸው ውጤት ሊያገኝ አለመቻሉን ታውቋል።
    የስርዓቱ ባለስልጣናት የሆነ ግለሰብ ከመሰለው ድርጅት ጋር በሰላማዊ መንገድ መታገልና መምረጥ በህገመንግስቱ ይፈቀዳል እያሉ በሚዲያዎቻቸው እየተናገሩ ቢሆንም በተግባር ግን በተቃራኒው ነው ሲሉ በርካታ የሃገራችን  ምሁራን በመግለጽ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።