Wednesday, August 12, 2015

በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ውስጥ የሚገኘው ህብረተሰብ በቂ ክፍያ ሳይሰጠው ቤቱ እየፈረሰ መሆኑ ታወቀ።



    በአማራ ክልል በባህርዳር ከተማ ውስጥ የቀበሌ 14 እና ቀበሌ 11 ውስጥ የሚገኘው የህዝቡ መኖርያ ቤት ለብዙ ዓመት ይኖሩበት የነበረውን ቤት ያለ ሕብረተሰቡ ፈቃድና ውይይት በዶዘር እየፈረሰ መሆኑን የገለጸው መረጃው ተበዳይ ህብረተሰቡ ወደ ሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በመሄድ ሰላማዊ ተቃውሞ ባደረገበት ሰዓት ደብድበው ማባረራቸውና ለተወሰኑትም ማሰራቸው የተገኘው መረጃ ገልጿል።
    መረጃው በማከል በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች የኑሮ ውድነት ሳያንሰን መኖሪያ ቤታችንን እንዲፈርስ መደረጉ የሞት ሞት ነው በማለት ብሶታቸውን እያሰሙ መሆናቸውና እስካሁን ድረስ ሰሚ የመንግስት አካል እንዳላገኙ ለማወቅ ተችሏል።