የደርሰን መረጃ እንዳመለከተው በአዊ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች ባለፈው ምርጫ
ላይ ሌሎች የተቃዋሚ ድርጅቶችን መርጣችኋል በሚልና አሁንም በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችን አላማ በግልፅ የሚደግፉ መሆናቸው
የሚታወቁ ዜጎችን አምባገንኑ ገዥው መንግስት በልዩ ሃይልነት ያቋቋማቸው
ቡድኖች ንብረታቸው በይፋ እየዘረፉ መሆናቸውን አስረድቷል።
መረጃው ጨምሮም ከተቋቋሙት ልዩ ሃይሎች መካከልም በጃዊ ወረዳ የደቅ
01 ቀበሌ ምክትል አስተዳዳሪ የሆነው አቶ አዳነ ክንፉ በአንከሻ ወረዳ በግብርናና ገጠር ልማት ፅህፈት ቤት ውስጥ በባለሙያነት
የሚሰራው አቶ ሃጤ እና በኮሶበር ከተማ የኦባማ ሆቴል ባለቤትና ሌሎችም ስግብግብ ግለሰቦች ገዥው መንግስት ለዘረፋ ያቋቋማቸው ልዩ
ሃይሎች አስተባባሪዎች መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ገልፁዋል።