የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው ገዥው መንግስት
ያሰማራቸው የሶማሌ ክልል ተወላጅ የሆኑ በአንዳንድ መስሪያ ቤት ውስጥ በሃላፊነት ቦታ ላይ የተቀመጡ አመራሮች የሌላ ክልል ተወላጅ
የመንግስት ሰራተኞችን ከነዋሪው ማህበረሰብ ጋር ያለውን ግንኙነት
በማሻከርና እርስ በእርስ በጥላቻ አይን እንዲተያዩ በማድረግ እየጨቆኗቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
ይህ እኩይ ተግባር በመፈጸም ላይ ከምገኑት የስርዓቱ ተላላኪዎች መካከልም የከተማው ዋና አስተዳዳሪና የከተማ ልማትና ቤቶች አስተዳደር ፅህፈት
ቤት ምክትል ሃላፊ የሆነው የክልሉ ተወላጅ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው
እያደረሰው ከሚገኘው በደልም ነዋሪውን ማህበረሰብ እየሰበሰበ የቤት
ኪራይ እንዳያከራዩአቸው ከተከራዩም የመብራትና የውሃ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ እንዲሁም በሚሰሩባቸው መስሪያ ቤቶች ሁሉ እንግልትና ጭቆና
እንዲደርስባቸው እያደረገ መሆኑን ታውቋል።
መረጃው ጨምሮም በደሉ ተባብሶ እየተካሄደባቸው ከሚገኙ ሰራተኞች መካከል
በንግድና ኢንዱስትሪ ፅህፈት ቤት የከተማ ልማትና ቤቶች አስተዳደር ፅህፈት ቤት በዙሪያ ወረዳዎች የሚገኙ በግብርና ፅህፈት ቤቶች
የሚሰሩ የአማራና የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።