Thursday, August 13, 2015

በአማራ ክልል የሚገኙት አርሶ አደሮች ማዳበርያ ውሰዱ እየተባሉ እየተገደዱ መሆናቸው ተገለፀ።



    ከክልሉ በደረሰን መረጃ መሰረት ማንኛውም የእርሻ መሬት ያለው አርሶ አደር ማዳበርያ የመግዛት ግዴታ አለበት በሚል የብአዴን አመራሮች ቀጥተኛ ትእዛዝ ህብረተሰቡ ክፉኛ እየተሰቃየና ትእዛዙ ያልተቀበለም እየታሰረ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
    በክልሉ ውስጥ በርካታ አርሶ አደሮች ማዳበርያ አልገዛችሁም ተብለው ከታሰሩት መካከል ከመርሳ ከተማ አቶ እንድሪስ፤ አቶ መኮነን ግዛው ከጎንደር፤ አቶ ባንተል ግዜ ከወልድያ እና ሌሎች ስማቸው ያልተገለፁ መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።