Thursday, August 13, 2015

መንግስት ወደ መከላከያ ሰራዊት አዳዲስ ወታደሮች በግዴታ እያስገባ መሆኑና ከክልሎች የተላኩት ምልምሎችም በሁርሶ ማሰልጠኛ እንደሰበሰባቸው ታወቀ።



    የኢህአዴግ መንግስት በአሁኑ ግዜ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ወጣቶችና ሴቶች የሚበዙበት ለተከታታይ ለሁለት ግዜ ያስመረቃቸው ምልምሎች በተለይ በተለያዩ የሞያ ስልጠና ትገባላችሁ ተብለው ወደ መከላከያ ዘርፉ የገቡት ሴት ወታደሮች በተዋጊ እግረኛ ሰራዊት በመመደባቸው ችግር ላይ መውደቃቸውና ሁኔታው በአመቱ ግምገማ ላይ ቢነሳም በቂ መልስ ሳይሰጥበት ስራቸውን እንዲቀጥሉ ትእዛዝ መሰጠቱን ተገለፀ።
    የስርዓቱ አመራሮች የተፈጠረውን የትጥቅ ትግል ተቃውሞ ከመጠን በላይ ስለአስጨነቃቸው ከተለያዩ ቦታዎች ወጣቱን በመልቀም ወደ ውትድርና አስገብተው በማሰልጠኛዎች ውስጥ አስገብተው የፖለትካ ትምህርት ቢሰጧቸውም ቅስቀሳቸው እንዳልተቀበሉት የተገኘው መረጃው አክሎ አስረድቷል።