Thursday, August 13, 2015

በምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫ ከተማ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ከተካሄደው ምርጫ ጋር በተያያዘ በገዥው መንግስት እንግልት እየደርሰብን ነው ሲሉ አቤቱታ ማቅረባቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



በምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫ ከተማ በተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤት ውስጥ የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች ባለፈው ግንቦት ወር 2007 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ ላይ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን መርጣችኋል በሚል ሰንካላ ምክንያት ገዥው መንግስት የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን እንዳናገኝ ተከልክለናል በተመሳሳይ ለክረምት ስልጠና ተመልምለንም ታግደናል በማለት አቤቱታ ማቅረባቸውን የደረሰን መረጃ አስረድቷል።
    መረጃው ጨምሮም አቤቱታ የቀረበለት የደንበጫ ከተማ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኤፍሬም በቅርቡ ያጋጠመንን የመብራትና የውሃ ችግር መፍታት ሳንችል ለሌላው ቃል መግባት ስለማልፈልግ ይህ ከአቅሜ በላይ  ስለሆነ ወደ ዞን አስተዳደር ፅህፈት ቤት ሄዳችሁ ጠይቁ የሚል ምላሽ የሰጠ ሲሆን የዞን አስተዳደርም እስካሁን ምንም ምላሽ እንዳልሰጣቸው ሊታወቅ ተችሏል።