ከገዢው
ሰረአት የበላይ አመራር አንዱ የሆነው በረከት ሰሞኦን ለጭልጋ ወረዳ
ነዋሪዎች በያዘነው ሳምንት ሰብሰባ በመጥራት። በዚህ አካባቢ የሚገኙ ቤተ እሰራኤውያን እርምጃ ልንወስድባቸው ሰለሆነ የአማራ ክልል
ተወላጆች የሆናቹ የሚወሰደዉን እርምጃ ለመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ
ለመዉጣት በተጠራችሁበት ጊዜ ወንድም ሆነ ሴት በሙሉ ተገኝታችሁ በሞራል በማውጣት መሳተፋ አለባችሁ
የሚል ያወረደው መመርያን ለአካባቢው ነዋሪ ሕብረተሰብ ወደ ግጭት የሚያስገባ መሆኑ ታወቋል።
የወረዳው ነዋሪ ህዝብ በበኩሉ እኛ ወገኖቻችን ሲጣሉ እናስታርቃለን እንጂ ይህ የምትሉትን መጥፎ ሃሳብ አንቀበልም ወደ ሰላማዊ ሰልፋ አንወጣም በማለት በህዳር 21 2008 ዓ/ም ታሰቦ የነበረ ሰልፋ ሳይፈፀም
የቀረ ሲሆን ነጋዴ ባህር በተባለ አካባቢ ለብዙ አመታት ሲኖሩ የቆዩ ቤተ እስራኤላውያን በብኣዴን /ኢህአዴግ አመራሮች ትእዛዝ እየተገፈፉ ወደ ሰደተኛች ካምፕ እየተሰበሰቡ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።