Saturday, February 27, 2016

ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ትህዴን ) ድርጅት የካቲት 19 የምስረታ ብአሉን ምክንያት በማድረግ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ!!



    በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ለሚገኘው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ፤ ጀግናው ሰራዊታችን፤ የድርጅታችን አባላትና ደጋፊዎች፣ እንኳን ለድርጅታችን የምስረታ በአል የካቲት 19 .15ኛው አመት አደረሳችሁ።
    ትጥቅ ትግል ሲባል፣ ከባድና መረራ ዋጋ የሚጠይቅ እንደሆነ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር የሚስተው አይኖርም። ምክንያቱም ተገድደህ የምትገባበትና የመጨረሻ አማራጭ ስለሆነ።
  ድርጅታችን ከ15 አመት በፊት የትጥቅ ትግሉን ሲጀምር፣ ህዝባችን የተታገለባቸውና ከባድ ዋጋ ከፍሎ ያገኘውን ድል ተነጥቆ ለጥቂት ግለሰቦች ጥቅም በመዋሉ ነበር።
    የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መሪዎች የህዝባችን ትግልና መስዋእትነት ተንተርሰው ስልጣናቸው ከተቆናተጡ በኃላ፣ የህዝቡ ፍላጎትና ጥቅም በማጨለም ህዝቡ እንዴት አድርጎ የትግሉ ተጠቃሚ መሆን አለበት ብለው ከማሰብ ይልቅ፣ እንዴት አድርገን ህዝቡን በማፈን የስልጣናችን እድሜ በማራዘም የግላችን ጥቅም እናረጋግጥ የሚል ፈሊጥ በመከተል፣ ለአመታት የተካሄደ የህዝብ ትግል ፍሬ ቢስ ሆኖ እንዲቀር አድርገዉታል።
    ድርጅታችን  ትህዴን በኢህአዴግ መሪዎች የተፈፀመውን የሚያሳዝንና የሚያስደነግጥ ክህደት፣ አንገትህን በመድፋት የሚፈታ ስላልሆነ፣ የመላው የኢትዮጵያ ህዝብና የሰማእታትን አደራ ለመመለስ፣ እንደገና የካቲት 19. 1993 ዓ/ም ትጥቅ ትግል እንዲጀምር ተገደዋል።
    የኢህአዴግ ስርአት በ25 አመታት የስልጣን እድሜው በህዝባችንና በአገራችን ላይ ስፍር ቁጥር የሌለው ወንጀሎች ሲፈፅም እንደቆየ የሚታወቅ ሲሆን፣ የከበደውና እጅግ የከፋው ደግሞ ህዝባችን ከመንግስታዊ ተቛማት ተገቢውን አገልግሎት አጥቶ አቤቱታውን ሲያቅርብ ምላሽ የሚሰጠው የመንግስት አካል በማጣቱ  ተስፋ በመቁረጥ ደም እያነባ በሚገኝበት በአሁኑ ጊዜ፣ ባለፈው ወር ግንቦት 2007 ዓ/ም የተካሄደውን አስመሳይ አገራዊና ክልላዊ ምርጫም ገዢው የኢህአዴግ ስርአት ራሱ ህዝባችን ለዘመናት አይቶትና ሰምቶት የማያውቀው ሰላምና ዴሞክራሲ በልማታዊ መንግስታችን ሊቋደስ በመቻሉ ምክንያት መቶ ከመቶ ድምፁን በመስጠት መርጦናል በማለት በህዝባችን ላይ ሲቀልድ ተሰምቷል።
  ይሁን እንጂ ድምፁን ለማን እንደሰጠ እያንዳንዱ መራጭ ሰለሚያውቅ በአነጋገራቸው ስይደናገር ከተካሄደው የይስሙላ ምርጫ በኃላ በመድርክ ላይ በግልፅ ስልጣኑን በማጭበርበር ነው የተቆጣጠራችሁት ነገር ግን የአስተዳደር ስርአታችሁ አስተካክሉ፣ ካልሆነ ግን ስልጣናችሁ ለህዝብ አስረክቡ በማለት በተቃውሞ መልክ ማሳለፊያ በከለከላቸው ጊዜ፣ ሳያፍሩ ህዝባችን በድምፁ የሰጠንን አደራ ለመመለስ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በሚል በመላው ኢትዮጵያ እያካሄዱት ያሉት ስብሰባዎች በመልካም አስተዳደር እጦት ትእግስቱን የጨረሰው ጭቁን  ህዝብ ለአንድ መቶ አመታት ያህል በመሩት ስርአቶች ያልታየ ትላልቅ ችግሮች፣ ባሳለፍናቸው 25 አመታት በህወሓት ኢህአዴግ ስርአት በሁሉም የአገራችን ክፍሎች  በንፁህ ህዝባችን ላይ የተፈፀሙ በደሎች እጅግ የሚዘገንኑ ናቸው።  በከፈተኛው የስልጣን እርከን የሚገኝ የበሰበሰው ቡድን ትተን በወረዳና በቀበሌ ያሉት ሹሞኞችና ሰራተኞች የተወሰኑ አመራሮች ከስልጣናቸው ማውረድና ማሰር ሊያሳዩ መሞከራቸው የብልሹ አስተዳደራቸው ማሳያ ሆኖ ይገኛል።
   ገዢው የኢህአዴግ ስርአት ነጋ ጠባ በሚድያዎቹ በማድረግ መልካም አስተዳደር ማስፈን በሚል ስብሰባ እያደረገ፣ ህዝቡን እያደነቆረ ያለውን ሁኔታ መጨረሻው ምን አይነት ውጤት ያመጣል ካልን ደግሞ፣ በተለየዩ የአገራችን አቅጣጫዎች እየተነሱ ያሉት ህዝባዊ ተቃውሞ አቅጣጫውን በማዞርና ለጊዜው ለመቀየር ካልሆነ በስተቀር የሚያመጣውን መፍትሄ ፈፅሞ ሊኖር አይችልም። ምክንያቱም የብልሹ አስተዳደሩ በሽታው ከግርጌው ሳይሆን ከራስ ጌው ስለሆነ፣ ራስ ጌውን እስካልታከመ ድረስ ግርጌውን ታክሞ የሚድን አይደለምና።
  ስለሆነም ነው ድርጅታችን ከበፊቱ ጀምሮ የህዝብ ውክልና የሌለው ስልጣን ላይ የሚገኝ አምባገነኑ ስርአት፣ የመላው ህዝባችንና አገራችን ጥያቄ ሊመልስ ይሁን በሰለማዊ መንገድ ከስልጣኑ ሊወርድ አይችልም በማለት ስለሚያምን፣ የመጨረሻ የሆነው አማርጭ የሌለው የትጥቅ ትግል ስልት ሊከትል የተገደደው።
   የተከበርክ የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ለአመታት ያህል ስታካሂደው የቆየሀው ትግልና ስትከፍለው የመጣሀው መስዋእትነት የአምባገነኖች ጥቅምና የስልጣናቸው እድሜ ማራዘሚያ ሲሆን፣ በአንፃሩ ደግሞ ያንተን መጨቆኛ ሆኖ ቆይተዋል።
    በስልጣን ላይ ያለው ፀረ ህዝብ ስርአት። ትናንት ሲገባልህ የነበረውን ውለታ በመካድ፣ ባንተ መስዋእትነት ስልጣን ጨብጦ በአፋኙ የመንግስት መረብ ካስገባህ 25 አመታት ያህል ያስቆጠረ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ በስብሶና አብቅቶለት ያለውን ስርአት፣ ከድራማዊ ምርጫው በኃላ ሌላ ድራማ“ መልካም አስተዳደር ለማስፈን” የሚል  ሞፎክር በመያዝ አንተን ስብሰባ በመጥራት በተለያዩ የማይተገበሩ ቃላት በማከማቸትና በማስፈራራት የስልጣኑ እድሜውን ለማራዘም የሚያደርገውን ተንኮልና ደባ ያብቃ እንድትለው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ትህዴን/ ጥሪዉን ያቀርባል።
  የተከበርክው ጀግናው ሰራዊታችን፣ ባለፉት 15 አመታት የትግል ጉዞ፣ በፀረ ህዝብ የኢህአዴግ ስርአት ላይ እየተጎናፀፍካቸው የመጣሀውን ትላልቅ ድሎች፣ የድርጅታችን እድገት በአሁኑ ጊዜ ደርሶት ያለውን ደረጃ ሊደርስ ችለዋል። አሁንም መፍትሄው ይዘሀው ያለውንና መስዋእትነት እየከፈልክበት የመጣሀው ትጥቅ ትግል ነውና፣ የህዝባችን ጥያቄ ለመመለስና የሰማእታትን አደራ ድሉን እንዲመታ ተልእኮህን እየፈፀምክ በነበርክበት ጊዜ፣ ባለፈው አዲስ አመት የተወሰኑት በትግሉ ጎራ የቆዩትን ግለሰዎች ግላዊ ጥቅማቸው ስለጎደላቸው፤ ትግሉ ለግላቸው በሚጠቅማቸው አኳሃን ሊጠመዝዙት ባለመቻላቸውና በአብዛኛው ተጋይ በመድረክ ላይ ስለተያዙ በዚህም የተነሳ ተስፋ በመቁረጥ ከትግሉ መስመርና ጎራ ተገፍትረዋል።
  የተከበርክ ጀግናው ሰራዊታችን በነዚህ አንተን የማይወክሉ ጥቂት ከጂዎች ጫና ሳይፈጥርብህ ከማንኛው ጊዜ በላይ ትግልህን ልትቀጥልበት ይገባሃል።
  የተከበራችሁ የአገራችን ተቃዋሚ ሃይሎች፣ አገራችን ኢትዮጵያ በአፋኙ ስርአት ስር ከገባች እነሆ 25 አመታት አስቆጥራ ትገኛለች። 25 አመታት ስልጣን ላይ በሚገኝ አምባገነኑ የኢህአዴግ ስርአት፣ በህዝባችንና በአገራችን ላይ ከፍተኛ ግፍና በደል ሲፈፅሙ ቆይተዋል አሁንም እየቀጠሉበት ይገኛሉ።
  በህዝባችንና በአገራችን እየደረሰ ያለውን አፈናና ጭቆና እንዲያበቃና እንዲቀጥል የምንወስነው እኛ በስርአቱ ውስጥና ብረት አንስተን በመታገል ላይ ያለን መሆናችን ግልፅ ነው። ምክንያቱም አላማችን ህዝባችን ከአፋኙ ስርአት ነፃ ማውጣት ቢሆንም፣ ሌሎቻችን የኢህአዴግ ተቃዋሚ ድርጅቶት በሰላማዊ መንገድ ሊወርድ እንደሚችል አድርገን የስልጣኑ እድሜ ማራዘሚያ ስንሆን፣ እኛ ትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ያለን ድርጅቶችም የነበረን ግንኝነት በማጠናከር የውህደት ጡንቻችን አጠናክረን ኢትዮጵያዊ ሃይል ፈጥረን በጠላታችን ላይ በትራችን የማናሳርፈበት ሁኔታ እየፈጠርንን እንገኛለን።
   ለመጠቃለል በአሁኑ ጊዜ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የምናደርገው ትግል አንድ አካል በመሆን ውጤት የሚያመጣ መንገድ ተከትለን ፀረ ህዝብና አገር የሆነውን ስርአት እድሜውን ልናሳጥረው ይገባል በማለት ድርጅታችን የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ እንኳን ለ15ኛው አመት የካቲት 19. 2008 ዓ.ም የምስረታ በአል አደረሳችሁ አደረሰን ለማለት ይወዳል።
የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ትህዴን )
የካቲት 19 2008ዓ/ም
ድል ለጭቁኖች!!

No comments:

Post a Comment