Tuesday, February 16, 2016

በጋምቤላ ክልል በኑዌር ብሔረሰብና በአኝዋክ ብሔረሰብ መካከል ያጋጠመው ግጭት ፒኙዶ ከተማ ዋና የግጭቱ መእከል መሆኗን መረጃው አሳወቋል።



የፊዴራል መንግሰት የኑዌር ብሔረሰብና የአኝዋክ ብሔረሰብን ለማሰታረቅ ከጋቤላ ከተማ ወደ ደቡብ አቅጣጫ 105 ኪ.ሜ ርቃ ወደ የምትገኘው ፒኙዶ ከተማ  በጥር 27 2008 ዓ.ም የሰብሰባ መደረክ ተከፍቶ እየተካሄደ በነበረበት ጊዜ፣ የኑዌር ብሔረሰብ በወሰዱት ደንገተኛ እርምጃ አንዲት እናት ከሁለት አመት ህፃን ልጅዋ ጋር ከገደሉት በኃላ፣ የፌዴራል መንግሰት ሁለቱን ብሔረሰቦች ለማረጋጋት ብሎ ያካሄደው ሰብሰባ በተነሳው ደንገተኛ እርምጃ ሰለ ተበተነ ግጭቱ ወደ ተባባሰ ሁኔታ መሄዱንና የገዢው ስርአት ወተሃደራት ግን ግጭቱን ከማረጋጋት ይልቅ የሚጨፋጨፈውን ህዝብ በአካባቢው ቆመው መታዘባቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
    ግጭቱን ለመቆጣጠር በማለት የፌዴራል ፖሊስና አግአዚ ክፍለ ሰራዊት ወደ ከተማዋ መግባታቸው ቢገለፀም እንኳ፣ ወጥረቱ ግን እሰካሁን ደረስ አለመብረዱን የተገኘው መረጃ ቢገልፅም፣ በተለይ የአኝዋክ ብሔረሰብ ተበድለናል በማለት የኑዌር ብሔረሰብ  በተጠለሉበት ሰፈራ በመሄድ በፈጠሩት ግጭት ሶስት የኑዌር ተወላጆች ሲገደሉ ከአኝዋክ ብሔረሰብ ደግሞ አንድ መገደሉ መረጃው ጨምሮ ኣስረድትዋል።

   በመጨረሻ የእንግሊዝ መንግሰትና ሌሎች የምእራባዊያን አገሮች በአካባቢው የተፈጠርውን ከባድ ግጭት ሰለአሰጋቸው ዜጎቻቸው ወደ ጋምቤላ እንዳይንቀሳቀሱ የማሰጠቀቂያ መመሪያ ማሰተላለፋቸውን ለማውቅ ተችሏል።  

No comments:

Post a Comment