Sunday, February 28, 2016

የእንግሊዝ ፤ ነርወይና የዩናይትድ ስቴት መንግስታት ዜጎቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ እንዳሄዱ የማስጠንቀቂያ ጥሪ እንዳስተላለፉ ተገለፀ።



ያገኘነው መረጃ እንደሚያመልክተው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል በመንግስትና በህዝቡ መካከል ተከስቶ ባለው ያለመረጋጋት የተነሳ በርከት ያሉት ወገኖች በኢህአዴግ ስርአት ታጣቂ ሃይሎች ህይወታቸው በመጥፋት ላይ በንመሆኑ፣ ህዝባዊ ተቃውሞን ስላልተረጋጋ ተጠናክሮ እየቀጠለ በመሆኑ ምክንያት የነርወይ፤ እንግሊዝና የአሜሪካ መንግስታት ዜጎቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ ወደ ኦሮሚያ ክልል እንዳይንቀሳቀሱ ለዜጎቻቸው የማስጠንቀቂያ ጥሪ አስተላልፈዋል።
እነዚህ አገሮች በተጨማሪም፣ ዜጎቻቸው ጥንቃቄ ኣንዲያደርጉና አዲስ ነገር ካለም መከታተል እንዳለባቸው በመምከር፣ በዚህ ሳምንትም በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሻሸሜኔና አጆን ከትሞች በተፈተረው ግጭት ምክንያት የአሜሪካ ኢንባሲ በከፍተኛ ሁኔታ በመስጋቱ የተነሳ ከአሁን ሰአት ጀምረው ኤሜሪካዊያን ዜጎች ወደ ተጠቀሱት አካባቢዎች እንዳይንቀሳቀሱ የማስጠንቀቂያ ጥሪ መስጠቱን ለማወቅ ተችሏል።

No comments:

Post a Comment