Sunday, February 28, 2016

ገዢው የኢህአዴግ ስርአት በመላው የኦሮሚያ ክልል የተከሰተው ተቃውሞ በቁጥጥር ስር አዋልኩት በሚልበት ጊዜ በተለያዩ ዞኖችና አካባቢዎች ተቃውሞውን ተባብሶ በመቀጠል ላይ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።



መረጃ እንዳስረዳው፣ ገዢው የኢህአዴግ ስርአት በሁሉም የኦሮሚያ ክልል ዞኖች የተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞ በቁጥጥር ስር አዋልኩት እያለ ባለበት ጊዜ በተለያዩ መንገዶችና አቅጣጫዎች የህዝቡን ተቃውሞ በከፍተኛ ሂኔታ በመቀጠል ላይ እንዳለ ከገለፀ በኃላ፣ በዚህ መሰረትም የካቲት 12 2008ዓ/ም በወለጋ ሆሮጉድሩ በተለይም በጀራቴ ወረዳና አሊቦ ከተማ ከፍተኛ የህዝቡ ተቃውሞ በመቀጠል ላይ እንደሚገኝ መረጃው አስረድቷል።
በሆሮ ጉድሩ ተቃውሞ እያሰማ ያለው ህዝብ ወደ መኪና መንገዶች በመውጣት መንገዱን በመዝጋት ወደ ከተሞች ለሚደረግ የመንግስት እንቅስቃሴ አስቸጋሪ አድርገዉት እንዳዋሉ ታወቀ።
ዘገባው በመጨረሻ፣ የህዝቡን ተቃውሞ ለመበተን በአካባቢው የሚገኙት ፌደራል ፖሊሶች ሰልፈኛውን ከበው በአርሶ አደሮችና ወጣቶች ክፍተኛ ጉዳት ቢያወርዱም እንኳ የህዝቡን ተቃውሞ ግን በይበልጥ በተጠናከረ መልኩ ሊቀጥል እንዳስቻለው መረጃው አክሎ አስረድቷል።

No comments:

Post a Comment