Wednesday, February 3, 2016

በኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ተቃውሞ አሁንም ተጠናክሮ እየቀጠለ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።



ባገኘነው መረጃ መሰረት፣ በወለጋ ዩንቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ የፌደራል ፖሊስ አባላት ዘለው በመግባት ተማሪዎችን በሚያነባ የጋዝ ጥይት፤ መብራት በማጥፋት፤ ጨለማ ተገን በማደረግ ወደ ተማሪዎች ዶርም በሃይል በመግባት በንፁሃን ወገኖች ላይ አሰቃቂ ድብደባ ኣንዳካሄዱ ታወቀ።
መረጃው ጨምሮ፣ በወለጋ ጉሊሶ፤ ጊዳሜ ቀሌማና ፤ ሆሮ ጉድሩ አመሩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤ በሰሜን ሽዋን የአባቴ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን በነቀምቴ፤ በወለጋ ዩንቨርስቲ ሃይለኛ ተቃውሞ ተነስቶ በአግአዚ የሚታወቅ ሰራዊት ደግሞ በተማሪዎች ላይ ጭካኔ በተሞላበት ደብዳብ እንዳካሂዱላቸው በመጥቀስ ከዚህ ሁኔታ ያመለጡት ተማሪዎች ደግሞ በአካባቢው የሚገኘው በርሃ በመሄድ ኣንደተደበቁና የተማሪዎች ተቃውምም በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በ1ኛ ሲሚስተር እየተፈተኙ በነበሩበት ጊዜ እጃቸውን ወደላይ በማንሳት ተቃውሞዋቸውን እያሰሙ እንደነበሩ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።  

No comments:

Post a Comment