በየካቲት19 /2008 ዓ/ም የተመሰረተው የትግራይ ህዝብ
ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ የ15ኛ አመት የምስረታ በአሉን በተለላዩ ኣከባቢዎች
በሚገኙ ሰራዊቶቹ በደማቅ ሰነ ስርአት እንደተከበረና፣
በዚሁ ክብረ በአልም የተለያዩ አጋር ድርጅቶች ተገኝተው ትግላቸውን ከትህዴን ጋር በመተጋገዝ አጠናክረው እንደሚቀጥሉና እንደዚሁም ደግሞ
ከውስጥና ከውጭ የመጡ የድርጅቱ ሲቪል ኣባላትም በበአሉ ተገኝተው ካለፈው በበለጠ ለትህዴን ያላቸውን ድጋፍና መተባበር ከማንኛውም
አጥናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።
በተጨማሪም ደግሞ ዝነኘዋ የትህዴን የባህል ቡዱን የተላለዩ የድርጅቱ
የትግል ጉዞንና ጥናትን የሚገልፁ ሰነ -ጥበባዊ ይዘት ያላቸው የትግል ወኔን የሚቀሰቅሱ ዜማዎች ድራማዎች ግጥሞችንና
ሌሎች ይዘት ያላቸው ቁም ነገሮች በሰራዊቱ ፊት በማቅረብ
ባሳየችው ዝግጅት ለበአሉ ተጨማሪ ድምቀት እንደሰጠው ለማወቅ ተችልዋል።
የተከበራችሁ
ተመልካቾቻችን የበአሉን አከባባር ሙሉ ዝግጅት በሚቀጥለው
ፕሮግራማችን ይዘንላችሁ የምንቀርብ መሆናችንን ከወዲሁ ልናስታዋሳችሁ እንወዳለን።
No comments:
Post a Comment