የአፍሪካ
አገራት በውጭ ኩባኒያና ኢንቨስተሮች አማካኝነትና በነዚህ አገሮች መሪዎች በማጭበርበር ገቢና ወጪ በማዛባት ገንዘብ ሆን ተብሎ በማጠፋፋት
በየአመቱ በቢልዮኖች ዶላር የሚቆጠር ሃብት የሚያጡት ለማቆም በሚል ተመሰረቶ በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኝ በደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት
ነበር ታቦ ኢምቤኪ የሚመራው ድርጅት፣ በዚህ ሳምንት ባካሄደው የፓነል ውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የአይ ኤም ኤፍ ባንክ መሪዎች
ኢትዮጵያ በዚህ ምክንያት ሃብት ከሚባክናቸው የአፍሪካ አገሮች አንዷ መሆንዋን የድርጅቶችሁ ሃላፊዎች መናገራቸውን ከወጣው መረጃ
ለማወቅ ተችሏል።
በደቡብ
አፍሪካ ፕሬዝዳንት ነበር ታቦ ኢምቤኪ የተመራው ውይይት ከአፍሪካ በተለያዩ መንገዶች በማጭበርበር በመጥፋት ላይ የሚገኝ ከፍተኛ
መጠን ያለው ገንዘብ በየ አመቱ ከ60 ቢልዮን ዶላር በላይ የሚገመት ይፋ በወጣው ጥናት ከማስቀመጡ በኃላ ይሁን እንጂ ባለፉት አምሳ
አመታት ውስጥ ከአፍሪካ በተጭበርበረ መንገድ የወጣውን ገንዘብ ከአንድ ትሪሊዮን ዶላር እንደሚገመት አስቀምጧል።
ቡዙ
ባለሞያዎችን ያሳተፈውን ትልቅ ይፋዊ የፓነል ውይይት የሆነውን ጥናት ኢትዮጵያ ከ2010 እ.ኤ.አ ጀምሮ በየ አመቱ ከ10 ቢሊዮን
ዶላር በላይ ገንዘብ ታክስ የማጭበርበር፤ የንግድ ገቢና ወጪ ማጭበርበር፤ የውጭና ገቢ ደረሰን ማስፈፀሚያ ሆን ብለው በማዛባት ወጪን
በማስበለጥና ሽያች በማሳነስ የመሳሰሉትን መንገዶች የሚጭበረበር ሲሆን፣ በዚህ ጉዳይ ደግሞ የመንግስት ባለ ስልጣናት በቀጥታ ይሁን
በተዘዋዋሪ እንዳሉትና ይህም ደግሞ ሳይታወቅ ተሸፋፍኖ በመሄዱ የአገር
ሃብት በማባከን ህዝብና የአገሪቱን በከፍተኛ ሁኔታ ኣየተጎዳች እንዳለች ሪፖርቱ ያስቀምጣል፣ ይሁንና ሪፖርቱ አግባብነት በሌለው መንገድ ሃብት ከተባከነባቸው 10 የአፍሪካ
አገራት ኢትዮጵያ በአንደኛ ደረጃ ጠቅሶ፣ እንዲሁም ናይጀሪያ፤ ግብፅ፤ ደቡብ አፍሪካ፤ ሞሮኮ፤ አንጎላ፤ አልጀሪያ፤ ኮት ዲቫር፤
ሱዳንና ዴሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ ሆነው፣ ከነዚህ ድሃ አገሮች ተጭበርብሮ የወጣውን ጠቅላላ ገንዘብ የሚቀበሉት 10 ሃብታም አገሮች
ደግሞ ኤሜሪካ አንዷ ስትሆን ቻይና፤ ህንድ፤ ፈርንሳይ፤ ጃፓን፤ ጀርመን፤ ደቡብ ኮሪያና ሜክሲኮ እንደሆኑ የጥናቱ ሪፖርት ያስቀምጣል።
No comments:
Post a Comment