Thursday, February 25, 2016

በትግራይ ክልል መረብ ለከ ወረዳ የሚገኙ ወጣቶች በስራ አጥነትና በመሬት ችግር ምክንያት በተለያዩ ማህበራዊና አኢኦኖሚያዊ ችግሮች እይተሰቃዩ እንዳሉ ተገለፀ።



በትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን መረብ ለከ ወረዳ የሚኖሩ ወጣቶች በስራ አጥነት፤ የመሬት ችግር  በተለይ ደግሞ የመልካም አስተዳደር ብከፋ መልኩ የታየበት ወረዳ በመሆኑ፣ መሬት ስጡን ብለው የጠየቁት ወጣቶች ጥያቄያቸው መሰረት በማድረግ መፍትሄ የሚያፈላልግ የአስተዳደር አካል በማጣታቸው የተነሳ፣ በአዲ ፍታው አካባቢ ሸቀጦችን ከፍተው ኖሯቸውን በሚመሩበት ጊዜ፣ ያላንዳች ማስጠንቀቂያና ዝግጅነት የአዲ ፍታው ቀበሌ አስተዳደር አቶ በየነ ተክልይና የቀበሌው የፀጥታ ሃላፊ የሆነው አቶ ገብረአበዝጊ ተኩሉና፣
 እንዲሁም የአዲ ፍታው ቀበሌ ምልሻ ኮማንደር የሆነው አቶ መብራህቶም ፍስሃ ፅዮንና ፖሊሶች በጋራ በመሆን ባለፈው ወር 50 የሚያህሉ በሸቀጣሸቀጥ የሚተዳደሩ ወጣቶች የመንግስት መሬት በራሳችሁ ፍቃድ ማን ስሩ አላችሁ በሚል ምክንያት፣ ስላስፈሯሩዋቸው ለከፋ ችግር በመጋለጣቸው አንዳንዶቹ ወደስደት ሲያመሩ፣ ሌሎች ወገኖች ደግሞ የመንግስት መሪወት ነው ከሚባለው ለቀው ወደ የግል አርሶ አደሮች መሬት ተጠግተው ኣንደሚገኙ አብራርተዋል፣
የንግድ ሸቆጦቻቸው ከፈረሰባቸው ወጣቶች ገሚሶችሁ ለመጥቀስ ያህል፦ ወጣት ተመስገን ( ወዲ ራያ )፤ ለተክርስቶስ ፀጋይ፤ ሸዊት ግርማይና ይብራህ ግርማይ እንዲሁም ሌሎች ከቡዙ በጢቂቱ እንደሆኑ በመግለፅ፣ ባጠቃላይ ደግሞ ለከፋ የኑሮ ችግር ተጋልጠው ኣንደሚገኙ ጨምረው አሳውቋል።  

No comments:

Post a Comment