Saturday, February 27, 2016

የኦሮሞ ህዝብን ተቃውሞ በመምራት ላይ ወጣቶች በህዝብ ንብረት ላይ ጉዳት ኣናደርስም ትግላችን ከአፋኙ ስር አት ጋር ነው እንዳሉ ታወቀ።



     የተገኘው መረጃ  እንደሚያመለክተው  በወጣቶች የሚመራው ተቃውሞ  ከግዜ  ወደ ጊዜ እየተባባሰ እንደሚሄድ የሚታወቅ ሆኖ በካቲት 12  2008 ዓ/ም  በሻሸመኔ ኣከባቢ ኣባሮ የምትባል ቦታ ለታቃውሞው የሚመሩ ወጣቶች ተሰብስበው በንፁሃን ዜጎች ሂወትና ንብረት ጉዳት ኣናደርስም  ትግላችን ከአፋኙ ገዥው የኢህ አዴግ ስርኣት ነው፣  በሚል የአንድነት ቃል ኪዳን ስምምነት መግባታትቸው ታወቀ።
   በአሁኑ ጊዜ በየቀኑ  በኦሮምያ ክልል የሚነሳው የህዝብ  ተቃውሞ  ስር አቱ   ግን ይህ ህዝባዊ ተቃውሞ  ሳይሆን   ሃይማኖትን ከለላ በማድርግ ፀረ ሰላምና ፀረ ልማት ሃይሎች የሆኑ  የውስጥና የውጭ ሃይሎች የሚመሩት ነው እያሉ በንፁሃን ወገኖቻችን በጥይት ሲገደሉና ወደ እስር ቤት እየገቡ ቢሆኑም  በዚህ ተግባር ህዝባዊ ተቓውሞው ሊገታ ስላልቻለ ከግዜ ወደ ግዜ ወደ ተባባሰ መልኩ እያመራ መሆኑን ታውቀዋል።
  በመጨረሻ  በኦሮምያ ክልል ተወላጆች በሆኑት ወጣቶች በካቲት 12 2008  ዓ/ም በሻሸመኔ በምትገኘው ኣብሮ በምትባል ቦታ የሚካሂዱት የአንድነት ስምምነት ቃል ኪዳን ለስርአቱ ትልቅ ፈተና ይሆናል ሲሉ የተለያዩ ሙሁራን ፖለቲካና ተንታኞች ይገልፃሉ።           


No comments:

Post a Comment