Friday, April 15, 2016

በሽሬ-እንዳስላሰ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ማረሚያ ቤት ከ3 ሺ በላይ እስረኞች ሞልቶ ባልበት፣ እስርቤቱ ለውሃ ችግር ተጋልጦ እንደሚገኝ ታወቀ።



  በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ሽሬ-እንዳስላሴ ከተማ የሚገኝ ማረምያ ቤት ከ3 ሺ በላይ እስረኞች በውስጡ ተጉሮው በሚገኙበት ግዜ፣ ከባድ የወሃ ችግር ኣጋጥሞት ስለሚገኝ፣ እስርቤቱ ችግሩ ከልክ በላይ ሁኖበት እንዳለ በከተማው የሚገኙ ምንጮቻችን ከላኩልን መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
በመሆኑም እስር ቤቱ ከአቅሙ በላይ እስረኞች በመያዙ የተነሳ እስረኞች በየቀኑ የሚጠጡትና ለፅዳት የሚሆን ውሃ በየ ቀኑ ባለማግኘታቸው ምክንያት፣ እሱረኞቹ ለተለያዩ ተላላፊ በሽታ እየተጋለጡ እንዳሉ በመግለፅ፣ በተጨማሪም ቤቶቹ ቀን በቀን የሚገባው የእስረኛ ቁጥር ሊያስተናግዱ ስላልቻሉ፣ ተጨማሪ ቤቶች በቆርቆሮ ሰርተው እስረኞቹ እያጎርዋቸው እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

No comments:

Post a Comment