በስልጣን ያለው ገዥው የኢህአዴግ ስርአት በቢልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ ተደርጎላቸው በመሰራት ላይ ናቸው የሚላቸው
ፕሮጀክቶች፣ ከፈተኛ ሙስና ተግባር የሚፈጸሙባቸው ተብለው በሞያተኞች እየተገለፀ ሲሆን፣ ይህ የሙስና ተግባር ሊቆም ከሆነ ደግሞ
የሚመለከታቸው አካላት የሚባሉት የጸረ ሙስናና የሰነ-ምግባር ኮሚሽን በዚህ ትኩረት አድርገው ሊሰሩ ይገባቸዋል የሚል ማሳሰብያ
በንግድ የሚተዳደሩት ዜጎች ባካሄዱት ስብሰባ ላይ እንደገለፁ ለማወቅ ተቻለ።
በስብሰባው ወስጥ በሞያተኞች ተዘጋጅቶ የቀረበ ጽሑፍ እንደሚያስረዳው፣ የጸረ ሙስና ኮሚሽኑ ችግሮች ከተፈጠሩ በኋላ
መንቀሳቀስ ሳይሆን የሚገባው የህዝብና የሃገር ሃብት ከመዝረፉ በፊት ለመከላከል የሚያስችል የሰነድ ዝግጅት መከታተል ስራው
እንደሆነ ሊያውቀው ይገባል ብለዋል።
በተለይ ደግሞ በትላላቅ ፕሮጀክቶች በተጨማሪም በመሬት
አስተዳደር ፣በግብር ፣በፍትሕ አሰጣጥ በአጠቃላይ በሙስና ምክንያት 40% የሚሆነው የመልካም አስተዳደር ጠንቅ መሆኑን በጥናት
የተደገፈ ሪፖርት ከተገለጸ በኋላ፣ በላይኞቹ መሪዎች በተግባር የተመሰረተ ክትትል በማድረግ ጥፋት ላይ በሚፈጽሙ አስተማሪ የሆነ
እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ራሳቸው በተግባሩ የተሰማሩ መሆናቸው ተገለፀ።
No comments:
Post a Comment