Friday, April 15, 2016

በቃፋታ ሑመራ ወረዳ የፍትሕ አካላት ተብለው የተቀመጡ ሰዎች በብልሹ አሰራር ዉስጥ በመዘፈቃቸው የሚገባ አገልግሎት እየሰጡ አይደሉም ተባሉ።



  በምንጮቻችን መረጃ መሰረት፣ በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ በሚገኙ የፍትህ ፅፈት ቤቶች ሰራተኞች ስልጣናቸው ተጠቅመው የሚሰሩ የገዢው የኢህአዴግ ስርአት ሽሞኞች፣ የስራ ሃላፍነታቸው ተገን በማድረግ፣ ጉቦ ለሰጠ አገልግሎት ሲሰጡት ግቦ ላልሰጣቸው ተገልጋይ ደግሞ የሚገባውን አገልግሎት በመከልከል የቆጠሮ ቀኖች እያራዘሙ ፍትሕ በማዛባት ስራ ተጠምደው ስለቆዩ፣ ህዝብ በዚህ ሳምንት ጠንካራ ግምገማ እንዳቀረበላቸው ለማወቅ ተችለዋል።
 በተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ የወረዳዋ አቃቤ ሕግ ሃላፊ ሆኖ ሲሰራ የቆየ ኢፍሬም ሃይለ የተባለ ግለ ሰው፣ በየቀኑ የሚሰራጨው ስራዎች ከግቦ ጋር የተሳሰረ ካልሆነ በስተቀር፣ ሕግ መሰረት ያደረገ ሕጋዉነት ያሟላ ስራ እንዳማይሰራ፣ የማይገባውን ሃብት ለመካበት ሕግ በመዛባት ተጠምዶ የቆየ ሰው በመሆኑ፣ በህግ ስር ዉሎ እንዲጠየቅ ህዝብ አስተያየት ስለቀረበ የመድረኩ መሪዎች ለግዜው በህግ ሲር እንዲውል ቢያድርጉትም፣ ነዋሪ ህዝብ ግን ሽሞኛውን የፈፀመው ጥፋት ተጣርቶ የሚገባው ቅጣት ያገኛል የሚል እምነት እንደሌላቸው ከመረጃው ለማወቅ ተችለዋል።

No comments:

Post a Comment