በቅርብ ቀን በጋምቤላ ክልል በንፁሃን ዜጎቻችን የደረሰውን አረመኔያዊ ጥቅት ተከትሎ በርካታ
ወገኖች የአንድ ሉዓላዊ ሃገር ድንበር ሊደፈር የሚችለውና ህዝቧም ለተለያየ ጥቃት ሊጋለጥ የሚችለው በሃገሪቱ ላይ ስለህዝቡ የማይቆረቆር
ስርዓት ካለ ህዝብ በተለያዩ ኃይሎች የጥቃት አደዳ ይሆናል ሲሉ ብዙ ወገኖች እየገለፁ እንደሚገኙ ተገልጿል።
ለአለፉት 25 ዓመታት በሃይል
በስልጣን ላይ የቆየውና አሁንም እየቀጠለ ያለው አፋኙ የኢህአዴግ ስርዓት የሃገራችንንና የህዝባችንን ጥቅምና ደህንነት በተደጋጋሚ
ለአደጋ እያጋለጠና እራሱ የአደጋው ፈጣሪ እየሆነ መጥቷል በማለት ዜጎች ስርዓቱን ቢነቅፉም እንኳ። ስርዓቱ ግን ዘላቂ መፍትሄ ከሚያመጣ
ይልቅ በተቃራኒው የስልጣን እድሜውን ለማስረዘም ሲል የህውከትና የብጥብጥ ተግባሮቹን እየፈፀመ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህ ሳምንት ከደቡብ ሱዳን በመጡ ታጣቂ ኃይሎች የተገደሉ ወገኖቻችን
በኢትዮጵያ የመንግስት አልባነት እንዳለ የሚያመላክት መሆኑን የገለፀው መረጃው በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ወገኖቻችንና ለሃገር
ደህንነት ለዴሞክራሲና ለሰብዓዊ የቆሙ ወገኖችና ድርጅቶች ይህንን አሰቃቂ ተግባር እጥብቀው ሊኮንኑት ይገባል ሲሉ ባለፈው ሳምንት
በርከት ያሉ ዜጎቻችን ሲናገሩ መሰንበታቸውን መረጃው አስረድቷል።
No comments:
Post a Comment