Wednesday, April 27, 2016

በአዲስ አበባ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ህጋዊ ያልሆነ ንብረት ህጋዊ አስመስለው የሚሰጡትን መንግስት ዝም ብሎ እየታዘበ ነው በማለት አቃቤ ህግ መክሰሱ ታውቋል።



በመረጃው መሰረት የቴክኒክ ጉዳይ አጣሪ ባለሙያ አበራ ገለታ 242 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው መሬት ከአገባብ ውጭ ለግለሰብ በመስጠት 656,425 ብር የህዝብና የመንግስትን ገንዘብ እንዳጠፉ አቃቤ ህግ ሲከስ የጉለሌ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ፅ/ቤት ኃላፊ ሙሉጌታ ስዩም ደግሞ ከፍርድ አፈፃፀም  የማገጃ ትዕዛዝ የተሰጡበትን ንብረት ከህግ ውጭ ለሌላ ግለሰብ እንዲያስረክቡ በማድረግ መንግስት ከፍተኛ ገንዘብ እንዲያጣ እንዳደረጉ በመግለፅ በክፍለ ከተማዋ በተለያዩ የስራ ኃላፊነት ላይ በነበሩ ሰዎች አቶ ሰለሞን ደስታ ፤ወርቁ ከበደ እና አባተ አራጋው ከአንድ ግለሰብ ጋር በመተባበር ንብረትነቱ የኪራይ ቤቶች የነበረን ቤት በመቀበል የማረጋገጫ ካርታ በመስራት ግለሰብ እንዲወስደው በማድረጋቸው 438,840ብር አጠፋፍተዋል በማለት አቃቤ ህግ ከሷል።
    ሌሎች የክፍለ ከተማዋ  የተለያዩ የስራ መስክ ኃላፊዎች ደግሞ አቶ አባተ አራጋው ፤እቶ ተሾመ ዓብይ፤ኢሳያስ ይታየው ፤አበራ ገለታና ትዕግስት አበበ ሁሉም በመተባበር ከ84.9 ሚሊዮን የሚገመት የህዝብና የመንግስት ንብረት የሆነውን  መሬትና ቤቶች አጠፋፍተው እያሉ መንግስት እያወቀ ዝምብሎ ሲመለከታቸው ቆይቶ በህዝቡ ትብብር ግን በአቃቤ ህግ ተከሰው ለግንቦት 3 እና 4 2008ዓ.ም በፍርድ ቤት ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል።

No comments:

Post a Comment