Sunday, April 17, 2016

የኢህአዴግ ገዥው ደርጅት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በየቀኑ ያለ መቋረጥ እየከዱ መሆናቸዉን የደረሰን መረጃ አመለከተ።



በምእራብና ደቡብ ምስራቅ እዝ ዉስጥ ባልደረባ የነበረዉና በሶማሌያ እንዲሁም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል እየተዘዋወረ እያገለገለ የሚገኝ መከላከያ ስራዊት፣ ገዥዉ ድርጅት በሜጀር ጄኔራል ኋየሎም አራአያ ወታደራዊ አካዳሚ ዉስጥ የስድስት ወር ብቻ የለብለብ የመኮንነት ስልጠና አጠናቆ ካመረቃቸው ምክትል መቶ አለቃ መላኩ አበበ ነጋሽ የኢህአዴግ ሰራዊት ተነጥሎ የሸሸ ሲሆን፣ ብዛት ያላቸዉ የሰራዊቱ አባላት ኢህአዴግን የማገልገል ፍላጎት እንደሌላቸዉና አጋጣሚዎችን እየተጠባበቁ በመጥፋት ላይ እነደሆነ ገልፀዋል።
  የኢህአዴግ ገዥው ቡድን አካዳሚዎች አንድ መኮንን አሰልጥኖ ለመመረቅ የሚወስዱትን እጅግ አጭር ግዜ ከመሆኑ አንጻር ምን ያህል የወያኔ መኮንኖች በብቃት እንደሚያገለግሉ እና ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናቱ በምን ያህል ግዜ የጄኔራልነት ቆቡን እንደሚጭኑት ለመገመት አመላካች መረጃ ሆኖ፣ እንደተገኘና የሰራዊቱን  የማማረር ሁኔታ በከፍተኛ  ደረጃ መደረሱን ለመረዳት ተችሏል።
 በመሆኑም በሐገር መከላከያ ሰራዊት ስም የኢህአዴግ ጥቅም አስጠባቂ አንሆንም! ያሉ በርካታ የመከላከያ ሹሞች መብቱን በሚጠይቀዉ ጭቁኑ ህዝባችን ላይ አፈ ሙዝ አንመዝም ሲሉ በመነጠል ላይ ሲሆኑ፣ በተጨማሪ የፖለቲካ አመለካከት የበላይነት የነገሰበት የሐገር መከላከያ አባል መሆን አያሻንም፤ የኢህአዴግ ባለስልጣናትን ኪስ ለማደለብ በሶማሌያ በከንቱ አንታረድም፤ ከሐገራችን ምድረ እርስት ላይ ተቆርሶ ለሱዳን መሬታችን ሲሰጥ ዝም ብለን አንመለከትም፤ ዝርፊያና ግፍ የነገሰበት ስርአት ጥቅም አስጠባቂ አንሆንም፤ በማለት ሰራዊቱ እየፈራረሰ መሆኑን  ገልፆ፣ በተለይም ሌላዉን የመጨፍለቅ እራይ ያለዉን የወያኔን ወታደራዊ ስልት ከመዋጋት አንጻር ሁሉም የመከላከያ አባልት የሚቻላቸዉን እርምጃ እንዲወስዱ አሳስበዋል

No comments:

Post a Comment