Monday, April 18, 2016

በአምቦ ዩንቨርስቲ ምንም ባላጠፋው ወንጀል ተደብድቦ ለአልጋ ቁረኛ የነበረው ወጣት ሕይወቱ ማለፉን የደረሰን መረጃ አስታወቀ።




በፈቶ ተደግፎ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው፣  ተክለ ቶማ  የተባለው  የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሶሽኦሎጅ ድፓርትመት 2 ኣመት ተማሪ ሲሆን፣ ህዳር ወር መጨረሻ አካባቢ በኣምቦ ዩኒቨርሲቲ በተነሳው የተማሪዎች ተቃውሞ ተያይዞ ምንም ባላጠፋበት ወንጀል አፍነው ከያዙ በኋላ የአጋዚ ወታደሮች ተራ በተራ እየተፈራረቁ ከፍተኛ ድብደባ አድርሰውበት፣ ላለፉት 4 ወራት የኣልጋ ቁረኛ ሆኖ ከቆየ በኋላ መጋቢት 24 /2008 ዓ/ም ህይወቱ ማለፍ ለማውቅ ተችሏል።
 ደማችን አንድ እስከሆነ ድረስ ሰብአዊ ፍጡር ሁሉ ይህንን አረመኔያዊ ድርጊት በጋራ ማውገዝ አለበት፣ የልጁ ቤተሰቦች ምንም አይነት መረጃ እንዳይሰጡ ከሞትና ከህይወት አንድ አንዲመርጡ የሚል ማስጠንቀቂያ ስለ ተሰጣቸው ዝም ብለዋል፣ ገዳዩች ለፍርድ እንዲቀርቡ፥ ምስኪን ቤተሰቦቹ ተገቢ ካሳ እንዲከፈላቸው በጋራ እንታገል የሚል አስተታያየትም ከአከባቢው ነዋሪዎች እየተነሳ እንደሚገኝ አክሎ የደረሰን መረጃ አመለከተ።

No comments:

Post a Comment