Wednesday, May 25, 2016

በኢትዮጵያ የኤለክትሪክ ሃይል ዘርፍ 16 አለም አቀፍ ኩባንያዎች መዋእለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ሲያካሂዱት የቆዩትን ድርድር በመቛረጡ ምክንያት ወደ ስርአቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቤቱታቸውን እንዳቀረቡ ታወቀ።



   የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው  ኢትዮጵያ የተለያዩ በሚሊዮን የሚገመት ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት  የገለፀው መረጃው፣ የሚመነጨው ሃይልም ከኢትዮጵያ አልፎ ወደ ሌሎች ሃገሮች ለመሸጥ የተለያዩ ስምምነቶች በስርአቱ እየተካሄደ የመጣና ያለ ነው ካለ በኋላ፣ 16 አለም አቀፍ ኩባኒያዎች በዘርፉ ማዋእለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ሲያካሂዱት የቆዩትን ድርድር በመቛረጡ ምክንያት፣ ግንቦት 13 2008ዓ/ም ወደ ስርአቱ ጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት አቤቱታቸውን እንዳቀረቡ ለማወቅ ተችሏል።
   ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አቤቱታቸውን ካሰሙ የውጭ ኩባኒያዎች ለመጥቀስ ያህል።- 4 የቻይና፤ 3 የአሜሪካ፤ 2 የካናዳ፤ 2 የደቡብ ኮሪያ፤ 2 የፈረንሳይ፤ 1 የቱርክ፤ 1 የኦስትሪያ፤ 1 የደቡብ አፍሪካ የሚገኙባቸው ሲሆኑ። እነዚህ የውጭ ኩባኒያዎች በኤሌክትሪክ ሃይል ዘርፉ መዋእለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የስምምነት ሰነድ ተፈራርመው የተለያዩ ጥናቶች እያካሄዱና እየተደራደሩ የቆዩ ሲሆኑ። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ቦርድ ሃላፊ በድርድር ሳይሆን በጨረታ መሆን አለበት በሚል ምክንያት በዘርፉ  ሲያካሂዱት የቆዩትን ድርድር ውድቅ አድረጎታል።
   እነዚህ የውጭ ኩባንያዎች እያካሄዱት የቆዩትን ጥናትና ድርድር ቡዙ ጊዜና የገንዘብ ወጪ እንደወሰደባቸው በመግለፅ የቦርዱ ውሳኔ ድጋሜ እንዲጠና በጥብቅ እንደጠየቁ መረጃው አክሎ አስረድቷል።

No comments:

Post a Comment