Wednesday, May 25, 2016

የሶማሌ ላንድ የገዥው ፓርቲ ፕረዝደንት የኢትዮጵያን መንግስት እንደወቀሰ ለማወቅ ተችሏል።



   የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው፣ ከአስር ወር በኋላ የሶማሊያ ፕሬዝደንት ሁነው ይመረጣሉ  ተብለው ትልቅ ግምት የተጣለባቸውና በአሁኑ ሰአት  የሶማሊ ላንድ ገዥው ፓርቲ  ፕሬዝዳንት የሆኑት ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሂ ኣብዲ  አገራቸው እንደ መንግስት በአለም ደረጃ እውቅና እንድታገኝ  ኢትዮጵያ የተቻላትን ያህል ኣልሰራችም በማለት እንደወቀሱ ታውቋል።
    ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ኣብዲ  ሶማሊያ ላንድ  ነፃና ራሷን የቻለች መንግስት ያላት አገር  ሆና እንዳትታወቅ ከሚያደርጉት ምክንያቶች  የጎረቤት አገሮች ናቸው በማለት ከገለፁ በኋላ ፣  በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያን መንግስት የወቀሱ ሲሆን፣ በዋነኛነት ኢትዮጵያን ሊወቅሱ የቻሉበት ምክንያትም፣ ኢትዮጵያ የሶማሌ ላንድ ታላቋ ጎረቤት ናት፤  ሶማሊ ላንድ  እውቅና እንድታገኝ ኣስተዋፅኦ ኣላደረገችም። እንደዚሁም  የአፍርካ ህብረት ፅህፈት ቤት መቀመጫ መዲና ሆና እያለች ሶማሊ ላንድ ገለልተኛ  እንድትሆን በመጣር ላይ ናት በማለት እንደወቀሱ ለማወቅ ተችሏል።







No comments:

Post a Comment