Wednesday, May 25, 2016

በመቀለ ከተማ የሚገኘው ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ከውስጡ በሚወጣው የቆሻሻ ፍሳሽ በአካባቢው ለሚኖሩ ህብረተሰቦች ከፍተኛ የጤና ብክለት እያስከተለ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።



    ከአይደር ሆስፒታል የሚወጣው ቆሻሻ ፈሳሽ ለረጅም ጊዜያት ያስቆጠረ ሲሆን ነዋሪው ህዝብ በእለታዊ ስራውና በማህበራዊ ህይወቱ እየደረሰበት ላለው ችግር ለሚያቀርባቸው አቤቱታዎችና ጥያቄዎች እስካሁን ድረስ ተገቢ ምላሽ ሊያገኝ ባለመቻሉ ምክንያት በአካባቢው የጤና ብክለት አስጊ ደረጃ ላይ ደርሶ እንዳለ ነዋሪዎች ለአይደር አካበቢ አስተዳደር ምሬታቸውን እየገለፁ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።
    የአይደር አካባቢ አስተዳደር ነዋሪዎች እንዳሉት በተበከለው ፈሳሽ ምክንያት ለተለያዩ በሽታዎችና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋልጠናል ሲሉ ከገለፁ በኋላ እለታዊ ኑሯችንን ለመምራት የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦችን ዘርግተን እንዳንሸጥ በተፈጠረው አካባቢያዊ ብክለት ምክንያት ለጤና አስጊ የሆነ ሽታ በመፍጠሩ ወደ እኛ መጥተው ሸቀጥ ይገዙ የነበሩ ደንበኞቻችን ለጤናቸው ስለሰጉ ለስራችን ትልቅ እንቅፋት ሆኖብናል ሲሉ ገልፀዋል።
    የሆስፒታሉ አስተዳደር በህዝብ ለቀረበለት አቤቱታና ጥያቄ ለችግሩ ተገንዝቦ መፍትሄ ከማስቀመጥ ይልቅ ለጊዜው ዝናብ ዘንቦ ከፈሳሹ ጋር ተደባልቆ ወደአካባቢው ሊፈስ ችሏል ቢሆንም ግን ደረሰ የሚባለው ችግር የተጋነነ አይደለም የሚል የማያረካ ምላሽ በመስጠቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ደግሞ በተሰጠው መልስ ተቆጥተው ለሚመለከታቸው የላይኞቹ አመራሮች ያመለከቱ ቢሆኑም እስካሁን ድረስ ትኩረት ሰጥቶ መፍትሄ ሊሰጥ ባለመቻሉ ለተደራራቢ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቀዋል።

No comments:

Post a Comment