Friday, May 27, 2016

ግንቦት 18 2008 ዓ/ም በአቶ ጌታቸው አሰፋ ይመራ የነበረ ስብስባ በድንገት ሊቋረጥ መቻሉን ተገለፀ።




     በተጠቀሰው እለት የኢህአዴግ  ተላላኪ   ከሆኑትና   ከብሄራዊ መረጃ የጠበቀ ግኑኝነት ካላቸው ግለሰቦች አምባሳደር ቀፀላ፣ የብሄራዊ  መረጃ ሃላፊ ከሆኑ ከአቶ ጌታቸው ኣሰፋ ጋር ስለ አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ በአርባ ምንጭ በወሰዱት ወታደራዊ ጥቃት ኣስመልክቶ ውይይት ይደረግ በነበረበት ግዜና፣ በተመሳሳይ በኮንሶ በመከላከያ ሰራዊት  በወሰዱት  ጥቃት  ከ55 በላይ የፖለቲካ እስ ረኞች ማውጣታቸውንና 19 ወታደሮች ደግሞ ሟችና ቁስለኛ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል።
    የተፈፀመውን  ጥቃት የሰማው ጌታቸው አሰፋ ደግሞ ተደናግጦ መድረኩን ትቶ  ሊወጣ እንደተገደደለማወቅ ተችሏል። አርበኞች ግንቦት ሰባት  በጎንደር ፤አርባ ምንጭና በሁመራ ጥቃት እንደፈፀመና  በተደረገው ውግያም  ከ24ተኛና ከ25ተኛ  ክፍለ ጦሮች  የተውጣጡ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል ከሚባሉት ወታደሮች በተደረገው ውግያ  ጉዳት እንደደረሰባቸውና  በፓርላማም ሳይቀር አነጋጋሪ ኣጀንዳ  እንደሆነ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።          

No comments:

Post a Comment